11.6 C
Addis Ababa
December23,2024
Homeየቅርብ ፅሁፎችመሠረተ ልማት ያለው ተቋም...

መሠረተ ልማት ያለው ተቋም የበለጠ ለማሳደግ በርካታ ምርቶች መምጣት አለባቸው

አቶ ኤርሚያስ እሸቱ፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ በቅርቡ የተሾሙት አቶ ኤርሚያስ እሸቱ የ41 ዓመት ጐልማሳ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት አቶ ኤርሚያስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ በኋላ ወደ ውጭ አገር በመጓዝ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ያጠናቁት እንግሊዝ አገር ነው፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከማንቸስተር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም በኮምፒውቲሽን ሲያገኙ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በዓለም አቀፍ ንግድ ትምህርት ወስደዋል፡፡ ከ20 ዓመታት በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁት በአይቢኤም፣ በአልካቴል፣ በኦሬንጅና በማክሮ ስትራቴጂ ኩባንያዎች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ሠርተዋል፡፡ ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ አገር ቤት መምጣት መጀመራቸውንና በ1991 ዓ.ም. አካባቢም ከቤተሰባቸው ጋር በመሆን በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ቢዝነስ ሥራ ውስጥ ሲሳተፉ ነበር፡፡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ መኖር የጀመሩት በ1994 ዓ.ም. ነው፡፡ ኑሮዋቸውን እዚህ ካደረጉ በኋላ ከሚሠሩት ቢዝነስ ጎን ለጎን ዘመን ባንክን ለማቋቋም በተደገረው ጥረት ውስጥ አሻራቸውን አስፍረዋል፡፡ በባንኩ ውስጥ እስከ ምክትል ፕሬዚዳንት ደረጃ ባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፣ ከታኅሳስ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሥራ ጀምረዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ባከናወኗቸው ሥራዎች፣ በተለይ በዘመን ባንክ ቆይታቸው ከዘመን ባንክ ወጥተው ወደ ምርት ገበያ እንዴት ሊገቡ እንደቻሉ፣ በምትር ገበያው ቆይታቸው ሊያከናውኑ ስላሰቡባቸውና ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ዳዊት ታዬ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ዘመን ባንክ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንና የተለየ የባንክ አሠራር ይዞ መግባት አለበት በሚል ተነስታችሁ የመሠረታችሁት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እንዳሰብነው ሆኖልናል ብለው ያምናሉ?

አቶ ኤርሚያስ፡- ዘመን ባንክ በሚመሠረትበት ወቅት ከአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጋር ተዋወቅን፡፡ ለባንኩ መቋቋምና ይዘቱ ምን መምሰል እንዳለበት የሐሳቡ ሻምፒዮን አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ነው፡፡ ለዚህም ምሥጋናውን መውሰድ አለበት፡፡ ለቴክኖሎጂው ጥሩ መድረክ ነበር የፈጠረው፡፡ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ ባንክ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሁኔታ ሲታይ እኔ ዛሬ ስለማስተዳድረው፣ እከሌ ደግሞ ነገ ስለሚያስተዳድረው ሳይሆን፣ በምክንያታዊነት በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ሊወዳደር የሚችል ባህል ያለው ባንክ እንዲፈጠር ለማድረግ ነው፣ ውጭ አገር የሚሠራበትን ነገር እንዲህ ቢሆንስ ተብሎ ነው የተነሳው፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል መድረክ ተፈጠረ፡፡ አዲስ ነገር አልተፈጠረም፡፡ በዚህ መድረክ የተፈጠረውን ሐሳብ ደግሞ የሚደግፉ ባለአክሲዮኖች ይህ ጥሩ ሐሳብ ነው ብለው በአጭር ጊዜ አክሲዮኖች ገዙ፡፡ በወቅቱ አክሲዮኖች ሸጠን የጨረስነው በሦስት ወራት ውስጥ ነበር፡፡ ስለዚህ ከዚህ ተነስተን የድርጅታችን አወቃቀር ስናየው ትርፋማነቱ በሁሉም ረገድ ተፈጥሯል ብዬ አምናለሁ፡፡ በኢንዱስትሪው ላይም በተወሰነ ደረጃ ለውጥ እንዲመጣና ቴክኖሎጂ ላይ መሠረት ያደረገ ሥራ ውስጥ እንዲገባ አድርገናል እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከእኛ ቀደሞ ኤቲኤም ነበረው፡፡ ግን አሁን ያለውን ሁኔታ ስታየው ሁሉም ባንኮች በቴክኖሎጂ ላይ ያለው አመለካከታቸው የበለጠ እየተለወጠ መጥቷል፡፡ በግሌ ኢንዱስትሪው ውስጥ ይታይ የነበረውን አሠራር እንዲለውጥ አስችሏል እላለሁ፡፡ አሁን ቆም ብዬ ሳየው ዕድል ሆኖ ለየት ባለ መንገድ ሥራ ውስጥ በመግባታችን ዕድለኞች ነን እላለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ከዘመን ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዴት ሊመጡ ቻሉ? ጥሩ እየሠራሁበት ነው ብለው ከሚያምኑት የዘመን ባንክ እንዴት ለቀቁ?

አቶ ኤርሚያስ፡- ግልጽ ለመሆን ከምርት ገበያው በኩል ያነጋገሩኝ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከስድስትና ከሰባት ወራት በፊት ለምርት ገበያው ይህንን ታስባለህ ወይ? በሚል መልክ ጥያቄው መጣ፡፡ ጥያቄውን ለመቀበል ብዙ ማውጣትና ማውረድ ነበረብኝ፡፡ ዘመን ባንክንም አስቤያለሁ፡፡ ዘመን ባንክ ያለው የሠራተኞች ጥምረት ደግሞ ጠንካራ ነበር፡፡ አብዛኞቻችን ለገንዘብና ለጥቅማ ጥቅም ብለን የምንሠራም አልነበርንም፡፡ በዘመን ባንክ ከምናገኘው በላይ ሊከፍሉን እንደሚችሉ በመጥቀስ በውጭና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ጭምር በተደጋጋሚ ጊዜ እንጠየቅ ነበር፡፡ እኛ ግን ባንኩ ይዞት የተነሳውን ራዕይ ማስቀጠል አለብን የሚል ፅኑ እምነት ስለነበረን ጥያቄውን አንቀበልም ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመቀበል ፈታኝ ነበር፡፡ እንዲህ እየሠራን የምርት ገበያውን ጥያቄ ለመቀበል ከባድ ነበር፡፡ የማይሆን ነገር ነው ብዬ ነበር የማስበው፡፡ ምርት ገበያውን ወክሎ የሚያናግረኝ ሰው ትንሽ አሳማኝ የሆኑ ነጥቦችን ይዞ ነበርና ነገሩን እንዳስብበት አደረገኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ምርት ገበያው እንዲመጡ ጥያቄ ከመቅረቡ በፊት ስለምርት ገበያው ምን ያህል ግንዛቤ ነበረዎት?

አቶ ኤርሚያስ፡- በአጋጣሚ ምርት ገበያውና ዘመን ባንክ አንድ ወቅት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2008 ዘመን ባንክ ሲመረቅ ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅን [የመጀመሪያዋ ዋና ሥራ አስፈጻሚ] የክብር እንግዳችን ነበረች፡፡ እኔም የዓለም አቀፍ ገበያ ግልጽ አሠራርን፣ የካፒታል ገበያ አሠራር ጠቀሜታን፣ የምርት ገበያ (ኮሞዲቲ ኤክስቼንጅ) የሚያመጣቸውን ነገሮች በዘመን ባንክ ውስጥ የምናስባቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የታቀፉ በመሆናቸው ጉዳዩን በደንብ አውቃለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ስለዚህ ከስድስት ወራት በኋላ ጥያቄውን ተቀበሉት ማለት ነው?

አቶ ኤርሚያስ፡- አዎ፡፡ ጉዳዩ እየተብላላ ሄዶ መጨረሻ ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ዘመን ባንክ ውስጥ ካሉት ባልደረቦቼ ጋር ተነጋገርኩበት፡፡ ትልቁና ፈታኙ ነገር ባልደረቦቼን ማሳመን ነበር፡፡ ዋናው ነገር ግን ወደዚህ የመጣሁት ጥቅም የተሻለ ነገር ኖሮ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- ደመወዝ የትኛው ይበልጣል?

አቶ ኤርሚያስ፡- አይደለም፡፡ ከመብለጥና ከማነስ ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡ ያ የግል ተቋም ነው፡፡ ከዚህ ጋር ማወዳደር ያዳግታል፡፡ እውነት ለመናገር ዓላማው እሱ አይደለም፡፡ በምንም አቅጣጫ ብታየው በዚያ እሳቤ የገባሁበት አይደለም፡፡ ነገር ግን ዶ/ር እሌኒና አቶ አንተነህ አሰፋ [ሁለተኛው ዋና ሥራ አስፈጻሚ] ከሄዱ በኋላ አዳዲስ ምርቶችን ወደ ምርት ገበያው ከማምጣት አንፃር በአገር ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ፋይዳና ሌሎቹንም ነገሮች ሳመዛዝን ወሰንኩ፡፡ በቃ በዘመን ባንክ በእውነት ጥሩ ሥራ ሠርተናል፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ጥሩ ሠርተን እዚህ አድርሰነዋል፡፡ ብቃት ያለው ተቋም ሆኗል፡፡ ከዚያ የተማርነውን ትንሽም ነገር ቢሆን ወደ ምርት ገበያው ይዞ መምጣቱ መልካም ነገር መሆኑ ስለታየኝ እንጂ ደመወዝ የሚለውን ነገር አላሰብኩም፡፡

ሪፖርተር፡- ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወጥተው ወደ ሥራ ዓለም ሲገቡ በመጀመሪያ ከተቀጠሩበት አይቢኤም ጀምሮ ሲሠሩ የቆዩት በግል ተቋማት ውስጥ ነው፡፡ አሁን ደግሞ እንደ መንግሥት ተቋም ወደ ሚቆጠረው ምርት ገበያ ገብተዋል፡፡ ከግል ወደ መንግሥት ሥራ መግባትዎ ምን ዓይነት ስሜት ይፈጥራል? እንዴትስ አዩት?

አቶ ኤርሚያስ፡- ለእኔ ብዙም የፈጠረብኝ ነገር የለም፡፡ ሥራው የመንግሥት ጉዳይ ነው፡፡ የሕዝብም ጥቅም አለው፡፡ ባንክ ውስጥም እኮ ስንሠራ እንደ ሥራ መሪ የሕዝብ ኃላፊነትን ጠዋት ማታ ትከሻህ ላይ ተሸክመህ ነው የምትሠራው፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ ሰብስበህ ነው የምትሠራው፡፡ ኃላፊነቱ እኩል ነው፡፡ እዚህም ሆነህ ስታየው የአሠራርና የቁጥጥር መዋቅሩ የምንሠራበት ነው፡፡ የግል ባንክ መባሉና ባለቤትነቱ በግለሰቦች መያዙን ያመለክታል እንጂ ያው የሕዝቡ አካላት ናቸው፡፡ የአሠራር ሥርዓቱ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡ ተጠሪነቱና ኃላፊነቱ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ ዓይነት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር እኔ ያየሁት የጎላ የተለየ ነገር የለም፡፡ እንዲያውም የተለየ የሚሆነው ሙሉ ለሙሉ ባለቤትነቱ በግል በተያዘ ተቋም ውስጥ ስትሆን ትንሽ ከፖሊሲ አውጪዎች ትርቃለህ፡፡ ግፊት ለማድረግና ለማስረዳትም የግል ከሆንክ ትርቃለህ፡፡ ምርት ገበያው ደግሞ የመንግሥትም ቢሆን በነፃነት የሚሠራ ተቋም ነው፡፡ ፋይዳውም ሰፊ በመሆኑ የበለጠ ንግዱ ላይና መሬት ላይ ያሉ ነገሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጉዳዮችን ከፖሊሲ አውጪዎች ጋር በመሆን የበለጠ ልትሠራበት ትችላለህ፡፡

ሪፖርተር፡- በየትኛውም ተቋም አንድ የሥራ መሪ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑ አይቀርም፡፡ የሥራ መሪዎች የየራሳቸው የአመራር ሥልትና ውጥን ይኖራቸዋል፡፡ አንድን ሥራ ሲጀምሩም ይህንን አደርጋለሁ ብለው ያስባሉ፡፡ ከዚህ አንፃር እርስዎ የምርት ገበያውን እንደሚመሩ ሲያረጋግጡ ለምርት ገበያው ምን የተለየ ነገር አደርጋለሁ ብለው አስበዋል?

አቶ ኤርሚያስ፡- ወደዚህ መምጣቴን ሳስብና በነገሩ ላይ ማሰላሰል ስጀምር በአጋጣሚ ከአገር ውጭ ነበርኩ፡፡ በነበርኩበት አገር ሳይቀር ገበያውን መመልከት ጀመርኩ፡፡ ሐሳቤ ሁሉ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ገበያው ውስጥ ያለው አስተማማኝ አቅርቦትና ግልጽነት የተሞላበት የምርቶች መሥፈርት በሙሉ በሌሎች የውጭ አገሮች የተሠራ ነው፡፡ በእውነት እኮ ምርት ገበያው ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ ምርት ገበያው ለዓለም አቀፍ ገበያ ብቻ ሳይሆን ለአገር ውስጥ ገበያም የሚሆን ትልቅ አቅም አለው፡፡ ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ የሚገበያይበት መድረክ ነው፡፡ ይህ ትልቅ ገበያ ነው፡፡ ለኤክስፖርት ብቻ ሳይሆን ለአገር ውስጥ ገበያ መረጋጋትም የሚጫወተው ከፍተኛ ሚና አለ፡፡ ለምሳሌ ገበያው ውስጥ ስኳር ይፈለጋል፡፡ ስኳር በኅብረተሰቡ ዘንድ በአንደኛ ደረጃ የሚፈለግ መሠረታዊ ምርት ነው፡፡ በቀን ውስጥ ስኳር ሳይቀምስ የሚያድር ሕዝብ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ የሚገበያይበትን መድረክ ግልጽና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ትልቅ ነገር ነው፡፡

የእኛ ኅብረተሰብ ደግሞ ከሌላው ዓለም የሚለይባቸው ነገሮች አሉ፡፡ በርበሬ፣ ጤፍና ቅቤ እንጠቀማለን፡፡ የእያንዳንዳችንን ጓዳ የሚነኩ ምርቶች አሉ፡፡ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ መውጣት ያለባቸውና በመንግሥት ፖሊሲ መገፋት ያለባቸው ምርቶች አሉን፡፡ ስለዚህ እዚህ ያለውንም ገበያ የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግ አለብን፡፡ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃም ስትሄድ ደግሞ በቀጣይነት የወጪ ንግድ ሚዛናችን እንዲጨምር ከማድረግ አንፃር (ግብርና ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ስለሆነ)፣ በዚህ ረገድ ልንጫወት የምንችለው ጥሩ ሚና አለ፡፡ ስለዚህ ተቋማዊ ጥንካሬያችንን በአስተማማኝ ሁኔታ መገንባት ይገባናል፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ሳትይዝ እንዲህ ላድርግ ወይም እንዲህ ያለውን ምርት ወደ ምርት ገበያው ላምጣ ብትል፣ መጋዘን ላለው ሠራተኛ ሊሸከመው የማይቻል ድንጋይ እንደማሸከም ነው የሚቆጠረው፡፡ ስለዚህ የግድ ተቋማዊ አሠራራችንን መገንባት ይኖርብናል፡፡ ጥሩ የሆነ አሠራር (ቼክ ኤንድ ባላንስ) ያስፈልገናል፡፡ ልክ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዳለው የሚገባውንና የሚወጣውን በሚገባ የሚከታተል፣ በቀጣይ ለሚፈጠሩ ገበያዎች ምሳሌ የሚሆን የአሠራር ሥልት ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

ዶ/ር እሌኒ ጥሩ ሥራ ሠርታለች፡፡ ጥሩ ዓይነት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተቋም ነውና ይህንን ብራንድ ወደ ገንዘብ መመንዘር አለብን፡፡ ለምሳሌ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ሁላችንም ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብዙ ጥሩ ነገር ሰምተናል፡፡ ይህንንም ይዘን አውሮፕላን አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ እንል ነበር፡፡ ምርት ገበያውንም እንደ ተቋም እንዲህ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በምርት ገበያው እየተገበያየ ያለው በቆሎ አምና በስንት ብር ተሸጠ? ዛሬስ በስንት ብር ይሸጣል? የምርቱን ብዛትና ጥበት በማመዛዘን ነገ ገበያው እንዲህ ሊሆን ይችላል በሚል መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ምርቱን በመደበቅና በመቅበር ሳይሆን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በገበያ ትንበያ ዙሪያ የሚሠሩ ባለሙያዎችን ማፍራት ይቻላል፡፡ እንዲህ ያሉ ሥራዎችን ጭምር በመሥራት ተቋሙን የበለጠ ማሳደግ ይቻላል፡፡

ሪፖርተር፡- እንደጠቀሱልኝና በተደጋጋሚ እንደምንሰማው ምርት ገበያው በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ ስም ተክሏል፡፡ ይሁን እንጂ የምርት ገበያው ውስጣዊ ይዘት የስሙን ግዝፈት ያህል አይደለም ይባላል፡፡ እርስዎ ተቋሙን ለመምራት ቦታውን ከተረከቡ ጥቂት ቀናት ቢቆጠሩም እንዲህ ዓይነቱን አስተያየት እንዴት ያዩታል? ምንስ ተገነዘቡ?

አቶ ኤርሚያስ፡- ይህንን ጥያቄ በሌላ መንገድ ልመልስልህ፡፡ እኔ የምቀበለው ነገር ምርት ገበያው ወደ ሥራ ሲገባ የሚያስደንቅ ፕሮጀክት ይዞ ነው፡፡ በመንግሥትም ደረጃ፣ በእነ ዶ/ር እሌኒም ጥረት፣ እዚህ ውስጥ በተሳተፉት ማኅበራት፣ በንግድ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣንና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ዘንድ ስትመለከተው ተቀባይነት ያገኘና ሻምፒዮን የሆነ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክት ደግሞ ከኤ ወደ ቢ የመድረስ ባህሪ ነው እንጂ ያለው፣ አንድ ቦታ ላይ ቆሞ የራሱን መዋቅር የመመርመር ዕድል ብዙ ጊዜ አያገኝም፡፡ ሰዎች የሚሉትን ነገር በተወሰነ ደረጃ የምቀበለው ምርት ገበያው ፕሮጀክት ተኮር እንጂ ተቋማዊ ብቃቱን ወደ መገንባት ያደላ አይደለም የሚለው ነገር ላያከራክር ይችላል፡፡ አሁን ባሉኝ የአሥር ቀናት ቆይታዬ ያለው እይታዬ ግን ጠንካራ የሆነ የባለሙያዎች ኃይል ያለን መሆኑን ነው፡፡ ከዚያ የማይተናነስ ተቋማዊ አቅም መገንባት አለበት የሚል አመለካከት አለኝ፡፡

ሪፖርተር፡- ምርት ገበያው ሲቋቋም በሥሩ ሊከናወኑ ይገባሉ የተባሉ ብዙ ነገሮች ነበሩ፡፡ ግን ሳይተገበሩ ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ ምርት ገበያው አሁን እያገበያያቸው ካሉ ምርቶች በተጨማሪ ሌሎችንም ምርቶች ያገበያያል የሚለው ነበር፡፡ ይህንን ሥራ ሲጀምሩ እንዲህ ያሉና ይሠራሉ ተብለው ያልተሠሩ ጉዳዮችን ሊፈትሹ ይችላሉ ብዬ ስለማምን፣ በምርት ገበያው ይገበያያሉ የተባሉ ምርቶች ለምን አልተጀመሩም? እርስዎስ የእነዚህን ምርቶች ግብይት ለማስጀመር ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አለ?

- A word from our sponsors -

spot_img

Most Popular

More from Author

Now is the time to think about your small-business success

The increase in overall pollution that the planet has seen during...

Program Will Lend $10M to Detroit Minority Businesses

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing...

Kansas City Has a Massive Array of Big National Companies

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing...

Olimpic Athlete Reads Donald Trump’s Mean Tweets on Kimmel

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing...

- A word from our sponsors -

spot_img

Now is the time to think about your small-business success

The increase in overall pollution that the planet has seen during the past few years has impacted the planet in such a way that it caused a ripple effect to happen in various domains. This is exactly why right now is the moment in which all of...

Program Will Lend $10M to Detroit Minority Businesses

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

Kansas City Has a Massive Array of Big National Companies

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

Olimpic Athlete Reads Donald Trump’s Mean Tweets on Kimmel

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

The Definitive Guide To Marketing Your Business On Instagram

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

Discover the Newest Waterproof and Fast Smartphones that Come on Sale

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

New Small Speaker Review: Pricing is Not Always the Only Criteria

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

Apple Electronics Climb the List of the Top Gadgets in Forbes Magazine

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

New Technology Will Help Keep Your Smart Home from Becoming Obsolete

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

The Hottest Wearable Tech and Smart Gadgets of 2022 Will Blow Your Mind

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

Things to Look For in a Financial Trading Platform Environment

I understand how that could positively effect your body, but alchemizing means turning elements to gold basically through magic. That lead me to research each ingredient because I know alchemy is not actually happening in my body when I eat this, since alchemy is not real. I...

The Secret to Your Company’s Financial Health is Very Important